Membership Payment

የቤተክርስቲያኑ አባልነትን በተመለከተ በመዝገብ ተመዝግቦ ያሉ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ብዙ ቢሆኑም ክፍያውን አጠናቆ ያሳለፍነውን ምርጫ መምረጥ የቻሉ አባልት ቁጥር ከሁለት መቶ የማይበልጡ ናቸው። በዚህም ምክንያት የቤተ ክርስቲያኑ ውርሃዊ ገቢ እጅግ የቀነሰ በመሆኑ በባንክ ያለው ገንዘብ የአንድ ዓመት የስራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈን የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሳል። ስለዚሀም አዳዲስ አባላትን ከመመዝገባችን በፊት ውዝፍ ያለባቸው አባላት ያለባቸውን ውዝፍ ከፍለው አባልነታቸውን የሚቀጠሉበትን አማራጭ ላይ ሰበካ ጉባኤው በሰፊው ከተነጋገረ በኋላ ከዚህ በታች ያሉትን ውሳኔዎች ወስኗል።

ምዕመናን አባል መሆንና አለመሆን ሁሉም እኩል አገልግሎት ስለሚያገኝ ጥቅሙን መረዳት አልቻሉም በሚል ለተነሳው አስተያየት በአንድ አጥቢያ የሚገኝ ምዕመን በሰበካ ጉባኤ አባልነት ተመዝግቦ መገኘት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የሚደነግገው ግዴታ መሆኑን ምዕመናን እንዲረዱት ማድረግ ፤ ትምህርት መስጠት አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ በቤተ ክርስቲያኑ ደንብ መሰረት ያለው መብትና ግዴታ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ተስማምቷል።
አባላቱ የረጅም ጊዜ ውዝፍ ስላለባቸው ቅነሳ በማድረግ ማበረታታት ይገባል በሚል በተነሳው ሃሳብ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቅናሾች ተግባራዊ እንዲሆኑ ተወስኗል።
ከ2013 በፊት እዳ ያለበት ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝለት
ከ 2013 – 2015 ያለው እዳ 50 በመቶ ቅናሽ እንዲደረግላቸው በሶስት ጊዜ ክፍያ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ እንዲከፈል
ከ 2016 ወዲህ ያለውን እዳ ሙሉ ክፍያ እንዲከፍሉ
አከፋፈሉን ለማብራራት ከ2010 ጀምሮ የረጅም ግዜ ውዝፍ ያለበት አንድ አባል ከ2016 ጀምሮ ያለበትን የ20 ወር ውዝፍ 200 ዶላር ቅድሚያ በመክፈል አባልነቱን በማደስ ፤ ከ2013 – 2015 ያለው እዳ 50 በመቶ 180 ዶላር በሶስት ጊዜ ክፍያ 60 60 ዶላር በዓመት ጊዜ ውስጥ እንዲከፈል ይጠበቃል