፳፻፲፮ ዓ.ም (2023-2024) ዘመን የሃይማኖት ትምህርትና የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ምዝገባ

  • ነባርም ሆነ አዳዲስ ተማሪዎች መመዝገብ ይኖርባቸዋል
  • ከ4 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ያሉ ልጆችን ለትምህርት እንቀበላለን
  • ከአንድ በላይ ልጅ የሚያስመዘግቡ ከሆነ ለእያንዳንዱ ልጅ የተለያየ ቅጽ ይሙሉ። አንድ ቅጽ ለአንድ ልጅ
  • ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ላሉ ተማሪዎች በሙሉ ትምህርት የሚሰጠው በሳምንት ሁለት ቀን ሲሆን ቅዳሜ እና እሑድ የሚኖሩን ክፍሎች (ትምህርቶች) በሙሉ የሚሰጡት በአካል በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ይሆናል። 
    • Pre-K and KG ክፍል ተማሪዎች የሚማሩት በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ሲሆን የትምህርት ክፍለ ጊዜያቸውም እሑድ ከቅዳሴ በኋላ ይሆናል።
    • አንደኛ እና ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች – ረቡዕ 6:30pm (virtual) እና እሑድ (በአካል) ከቅዳሴ በኋላ
    • ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ ክፍሎች በሙሉ – አርብ 6:30pm (Virtual) እና ቅዳሜ 11am (በአካል)ይሆናል። 

የመመዝገቢያ ቅጹ በትክክል መሞላቱን እንግጠኛ ይሆኑ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።
መመዝገቢያ ቅጽ: https://forms.gle/4iQRxVvbufjUHZ7x5

የቦታው ግዢ በስኬት ተጠናቀቀ

ከሐምሌ መጀመሪያ ጀምሮ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግበት የነበረው ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ያለውን የፓርኪንግ ቦታ እና ቤቶች የመግዛት ሂደት ረቡዕ ኅዳር ፳፩ በእመቤታችን ዕለት በስኬት ተጠናቋል። የዲሲ እና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ፣ የሰበካ ጉባኤው አባላት ፣ የማውንት ኮሬብ ባፕቲስት ቸርቺ ቦርድ አባላት እና የሁለቱም የሪል ስቴት ባለሙያዎች በተገኙበት በዋሽንግተን ዲሲ ዲስትሪከት ታይትል ካምፓኒ ጽሕፈት ቤት የፊርማ ስነ ሥርዓት ተከናውኗል። ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ዕድገት ትልቅ ምዕራፍ ሲሆን የኧርል ፕሌስን አንድ ጎን ሙሉ ይዞታ እና የዋናው መንገድ ገጽታ ጭምር እንዲያገኝ ዕድል የሰጠ ነው። በዚህ የግዢ ሒደት ላለፉት አምስት ወራት ከአቅማቹ በላይ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ፣ በጸሎት በማገዝ ፣ በሐሳብ ፣ በሥራ በማገዝ የበኩላች ሁን ለተወጣች ሁ ሁሉ ዋጋን የማያስቀር እግዚአብሔር እጥፍ ድረብ አድርጎ እንዲሰጣች ሁ እንመኛለን። አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የተመሰገነ ይሁን።

ለሚገዛው ቦታ ፈንድሬዚንግ

ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል (ዋሽንግተን ዲሲ)ከቤተ ክርስቲያኑ ጎን ለሽያጭ የወጣውን የፓርኪንግ ቦታ እና ሦስት ቤቶች ከ፫ ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጎ ለመግዛት እያደረገ ላለው ጥረት የተዘጋጀ ፈንድሬዚንግ ነው። ከማክሰኞ ኅዳር ፮ (November 15) ጀምሮ በፌስ ቡክ ዶኔሽን ወርሃዊ ክፍያ ለሚያደርጉ ፌስ ቡክ ሁለተኛ ክፍያቸውን እስከ መቶ ዶላር ድረስ እጥፍ(ማች) በማድረግ ይሰጣል። ስለዚህ በወር እስከ መቶ ዶላር ድረስ የአቅሞትን ይለግሱ። ፌስቡክ ለዶኔሽኑ ምንም አይነት ክፍያ አያስከፍልም። ለሚያደርጉት ትብብር እናመሰግናለን።

It is a fundraising for the effort of Debre Mihret St Michael Cathedral (Washington DC) to buy the parking lot and three houses that are for sale next to the church for more than 3 million dollars. Starting from Tuesday November 15, for those who make a monthly donation on Facebook, Facebook will double their second payment up to a hundred dollars. So donate what you can afford up to a hundred dollars ($100) a month. FACEBOOK WILL NOT CHARGE YOU ANYTHING FOR THE DONATION. Thank you for your cooperation.

በፌስ ቡክ ዶኔት በማድረግ ማቺንግ ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን መመሪያ ይከተሉ

  1. ከዚህ በታች ያለው ሊንክ ይጫኑ

https://www.facebook.com/donate/1764205667298256/

2. የገንዘቡን መጠን መቶ ዶላር ወይም እንደ አቅሞት ከዚያ በታች ያስገቡ በመቀጠል በየወሩ(Monthly) የሚለውን ይምረጡ

3. ከዚህ በፊት ካርድ ካስገቡ ካርዱን ይምረጡ ወይም የካርዶን መረጃ ያስገቡ

4. ከታች ያለውን ዶኔት (Donate $100) የሚለውን ቁልፍ (Button) ይጫኑ

የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ

የቤተ ክርስቲያናችን አባላት ጠቅላላ ጉባኤ የፊታችን አርብ የካቲት ፳፮ (Mar 5, 2021 6PM) በዙም የሚደረግ ሲሆን በዚሁ ቀን በያላችሁበት ሆናችሁ በኦን ላይን እንድትሳተፉ እናሳስባለን።

Zoom Meeting ID: 324 600 1410

Pass Code: 33 62 23

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን!!!!!

በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካቴድራል የጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን እንላለን!!!!

እንደሚታወቀው ሰንበት ትምህርት ቤታችን በዛሬው ዕለት በጌታ ትንሣኤ ከካህናት አባቶቻችንን ጋር የቆየ የምሳ መርሐ ግብር ልማድ ነበረን። ሆኖም ዓለምን ባስጨነቀው ወረርሺኝ ምክንያት እንደ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን መርሐ ግብሮች እንደተለመደው ማካሄድ አልተቻለም። በመሆኑም እግዚአብሔር በምሕረቱ ጎብኝቶን ወደ ቀደመ ወደምንናፍቀው አገልግሎታችን እንዲመልሰን እየተማጸንን ይህቺን አጭር መልክእት በአባላቱ ስም እናስተላልፋለን።

የ2020 የደብረ ዘይት በዓል

የ2012 ደብረ ዘይት በዓል በኮሮና ወረርሺን ምክንያት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል እንደ ሎሎቹ የዲሲና አካባቢው አብያተ ክርስቲያናት መንግሥት ባወጣው የብዙኀንን መሰባሰብ በሚያግደው መመሪያ መሠረት ለአገልግሎት በመዘጋቱ ቅዳሴው በካህናት ብቻ ተከናውኖ ለምዕመኑ በድረ ገጽ ቀጥታ ስርጭት ከኪዳን ጀምሮ እስከ ስብከተ ወንጌል የነበረው አገልግሎት ተላልፏል።ይህ በቤተ ክርስቲያኑ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ከአቅም በላይ በሆነ አየር ንብረት ማለትም ከከባድ በረዶ መውረድ ውጪ የቤተ ክርስቲያኑ(ካቴድራሉ)ለአገልግሎት ለምዕመናን ክፍት ያልሆነበት ጊዜ ይህ የመጀመርያው ነው። ይህ ክስተት ማለትም ወረርሺኙ እስከ አሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር ያልሆነ ስለሆነ ምዕመናን መች ተመልሰው በቤተ ክርስቲያን በአካል ተገኝተው አገልግሎት መካፈል እንደሚችሉ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው መንግሥታዊ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች ሁሉ ተዘግተዋል አሊያም አገልግሎት ቀንሰዋል። በመላው የተባበሩት አሜሪካ ግዛቶችም ያሉ ሕዝብ ሁሉ በዚህ ዓይነት ሁናቴ ላይ ይገኛሉ።
በመሆኑም ለሚቀጥሉትም ሳምንታት ይህ መሰሉ አገልግሎት እንደሚቀጥል ይታመናል። ልዑል አምላክ በይቅርታው ተመልክቶ መፍትሔ እንዲሰጠን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን!

 

መጋቢት ቅዱስ ሚካኤል ቅዳሴ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ምዕመናን በቤታችን ሆናችሁ እንድታሳልፉ መንግስት ማስጠንቀቁ ይታወሳል። በዚህ ምክንያት ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባት ባይቻልም ካህናት ወደ እግዚአብሔር በመለማመን ጸሎት ቀጥላዋል። የዛሬ መጋቢት ቅዱስ ሚካኤል ቅዳሴ በፌስቡክ ገጻችን እናስተላልፍላችኋለን።

የዛሬ ቅዳሴን ከዚህ በታች ያለውን ምስል በመጫን ይከታተሉ።

Facebook link

https://www.facebook.com/groups/35778443673/

Youtube link

https://youtu.be/uPmu8sJGkj0

የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ልዩ ማሳሰቢያ

የተወደዳችሁ የደ/ም/ቅ/ ሚካኤል ካቴድራል አባላት በያላችሁበት ሰላመ እግዚአብሄር ይድረሳችሁ!

የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ወረርሽኙ ትልቅ ስጋት በመሆኑ በዲሲ ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ግዛቶች የአደጋ ጊዜ አስቸኳይ አዋጅ ከመታወጁም በላይ ትላንት ማምሻውን አዋጁ በመላ ሀገሪቱ ሁሉ እንዲሆን ተወስኗል። በዚህ መሰረት የሃገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ በሰጡት መንፈሳዊ መመሪያና ቦርዱም ባለፈው እሁድ አሳሳቢነቱን እያየን ውሳኔዎች እናስተላልፋለን ባለው መሰረት ወረርሽኙን ለመከላከል እንዲቻል ውሳኔ ተላልፏል:: ይህም ምዕመናን ሁሉ ከዛሬ ቅዳሜ 03/14/2020 ጀምሮ ከነቤተሰቦቻችሁ ለሚቀጥሉት 3 እሁዶች በቤታችሁ ሆናችሁ በጾምና በጸሎት ይህንን ክፉ ጊዜ እንድታሳልፉ ተወስኗል:: ለዚሁ ተፈጻሚነት ሁላችንም በየቤታችን ሆነን የሱባኤውን ጊዜ በፆም በፀሎት ተጠምደን ከ3 እሁዶች በኋላ እንድንገናኝ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።  የሀገረ ስብከቱን መመሪያም ከዚህ በታች ማያያዛችንን እንገልጻለን።


የእግዚአብሔር ጥበቃውና ረድኤቱ
ከሁላችን ጋር ይሁን !

የደ/ም/ቅ/ ሚካኤል ካቴድራል አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ (ቦርድ)