Donate

ቤተ ክርስቲያናችን የመኪና መቆሚያ ማስፋፊያ እና ተጨማሪ ሦስት አሮጌ ቤቶች ያሉበት ግማሽ ኤከር መሬት በ2.9 ሚሊዮን ዶላር ገዝቶ በወር 15 ሺ ዶላር ሞርጌጅ እየከፈለ ሲሆን ቤቶቹን በፍጥነት አሳድሶ የልጆች ማስተማሪያ ሁለገብ አዳራሽ ለመገንባት ያስባል። ይህንን ጥረት ለማገዝ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ አደራ እንላለን።

ለቤተ ክርስቲያናችን አባላት እና ምዕመናን ለቤተ ክርስቲያን ስጦታ ፣ መባ ፣ አስራት ወይም ስለት ኦን ላይን መስጠት ከፈለጉ ከዚህ በታች ያለውን “ለቤተ ክርስቲያኑ ይለግሱ” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ ስኴር የመክፈያ በመሄድ የአቅሞትን መለገስ ይችላሉ።

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች

እግዚአብሔር ረድቶን ባለፈው ዓመት ለፋሲካ አንድ ኩንታል (a quintal for Fasika) የሚል ዘመቻ ተጀምሮ ከ$36,000 በላይ ሰብስበን ከግማሽ ሚሊዮን ኩንታል በላይ እህል ከቅዱስ ሚካኤል በጎ አድራጎት ከየቦታው: ተፈናቅለው: በደብረ ብርሃን ለሰፈሩት ተፈናቃዮች ተበርክቷል:: 

እንዳውም ትርፍ ገንዘብ ኖሮን: 5 ለእርድ የሚሆኑ በሬዎችን: ዘይት: እና: 500 ብርድ ልብሶች: በጎ አድራጎት: አስረክቧል::

በአሁኑ ሰዓት ችግሩ በጣም የተባባሰ ቢሆንም: በዚህ ዓመትም እንዳለፈው  ዓመት አንድ ኩንታል ለፋሲካ እንድታበረክቱልን የቅዱስ ሚካኤል በጎ አድራጎት ክፍል በአክብሮት ይጠይቃል

አንድ ኩንታል ለማትችሉ ግማሽ ኩንታል መለገስ ትችላላችሁ 

ጤፍ – $130 
በሶ –  $140
ምጥን ሽሮ – $140
ስኳር $130
ስንዴ – $100
ሽንብራ – $100
ብርድ ልብስ – $40

እርዳዋትን ከዚህ በታች ያለውን ስኵር ሊንክ በመጠቀም መላክ ይችላሉ።