የተወደዳችሁ ምዕመናን በኮቪድ ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ለማግኘት የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሳሰቢያዎች ተመልክተው ፤ በመመሪያው መሰረት ይመዝገቡ።
1. ክርስትና ለማስነሳት በጽሕፈት ቤቱ ስልክ በመደወል ቀጠሮ ያስይዙ። ክርስትና የሚያስነሱ ለመግባት የሚፈቀድላቸው አባት ፣ እናትን እና የክርስትና አባት ወይም እናት (በቁጥር ሦስት ) ብቻ ይሆናል።
2. ለመጀመሪያ ጊዜ ሥጋ ወደሙ መቀበል የሚፈልጉ በንስሐ አባታቸው በኩል ከ10 ቀን በፊት ለጽሕፈት ቤት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል
3. ምዕመናን ጸሎተ ቅዳሴ በኦን ላይን የሚተላለፍ ሲሆን በአካል መጥተው ማስቀደስ ሲፈልጉ ከዚ በታች ያለውን ፎርም ለእሁድ አገልግሎት ለተመዘገቡ ምዕመናን በተመዘገቡት መሠረት ተራቸው ሲደርስ ይሰጣል።
4. ተመዝግበው ለማስቀደስ መምጣት የሚችሉት ተደውሎ ሲጠሩ ብቻ ነው።
5. አንድ ጊዜ ከተመዘገቡ በቂ ነው። ድጋሚ የተመዘገበ ከተገኘ የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
6. አባላት 80% ሰማኒያ በመቶ አባል ያልሆነ ደግሞ 20% በመቶ ብቻ እድል ስለሚሰጥ የአባልነት ቁጥሮን ማስገባት ተገቢ ነው። ትክክለኛ የአባልነት ቁጥር ያላስገባውን ቅጹ እንደ አባል አይቆጥረውም
7. ዕድሜው ከ5 ዓመት በላይ የሆነ ልጅ ሁሉ ስለሚቆጠር ለብቻ መመዝገብ ይኖርበታል
በቅዳሴ አገልግሎት ለመሳተፍ ለምትፈልጉ የምዝገባ ቅጽ በቅዳሴ አገልግሎት ለመሳተፍ ምዝገባ እዚህ ይጫኑ