ወደ ዋና ገጻችን እንኳን በደህና መጡ!
Welcome to our church web site!
ካቴድራላችን ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን መተዳደሪያ ደንብ በአዲስ ለመቀየር እና የሚቀጥሉትን ሰበካ ጉባኤ አባላት መርጦ ለማስረከብ እየሰራ ይገኛል። በዚህ ሂደት የካቴድራላችን አባላት ንቁ ተሳታፊ በመሆን በመተዳደሪያ ደንቡን በማጽደቅ ላደረጋችሁት ርብርብ ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን።
ጠቅላላ ጉባኤው መጋቢት ፲፬ (March 23, 2025) በከፍተኛ ድምጽ (በአስር ድምጽ ተቃውሞ ብቻ) የቀድሞው መተዳደሪያ ደንብ በቀረበው አዲስ ድራፍት መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ላይ አስተያየት ተካቶበት ለድምጸ ውሳኔ በአስቸኳይ እንዲቀርብ በወሰነው መሰረት የመተዳደሪያ ደንቡን ለማጽደቅ ልዩነት ባለባቸው ነጥቦች ላይ እሁድ መጋቢት ፳፰ (April 6, 2025) ፣ ሚያዚያ ፭ (April 13) ፣ ሚያዚያ ፲፱ (April 27) ለሦስት ሰንበቶች ድምጽ ተሰጥቶበት ድምጽ ከሰጡ 368 አባላት ከ95 በመቶ በላይ እንዲጸድቅ ወስኗል። በሚያዚያ 2017 (April 2025) ጸድቆ አገልግሎት ላይ ያለውን የካቴድራላችን መተዳደሪያ ደንብ ከዚህ በታች ያለውን መጠቆሚያ በመጫን ማግኘት እንደሚችሉ እናሳስባለን።
