የቦታው ግዢ በስኬት ተጠናቀቀ

ከሐምሌ መጀመሪያ ጀምሮ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግበት የነበረው ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ያለውን የፓርኪንግ ቦታ እና ቤቶች የመግዛት ሂደት ረቡዕ ኅዳር ፳፩ በእመቤታችን ዕለት በስኬት ተጠናቋል። የዲሲ እና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ፣ የሰበካ ጉባኤው አባላት ፣ የማውንት ኮሬብ ባፕቲስት ቸርቺ ቦርድ አባላት እና የሁለቱም የሪል ስቴት ባለሙያዎች በተገኙበት በዋሽንግተን ዲሲ ዲስትሪከት ታይትል ካምፓኒ ጽሕፈት ቤት የፊርማ ስነ ሥርዓት ተከናውኗል። ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ዕድገት ትልቅ ምዕራፍ ሲሆን የኧርል ፕሌስን አንድ ጎን ሙሉ ይዞታ እና የዋናው መንገድ ገጽታ ጭምር እንዲያገኝ ዕድል የሰጠ ነው። በዚህ የግዢ ሒደት ላለፉት አምስት ወራት ከአቅማቹ በላይ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ፣ በጸሎት በማገዝ ፣ በሐሳብ ፣ በሥራ በማገዝ የበኩላች ሁን ለተወጣች ሁ ሁሉ ዋጋን የማያስቀር እግዚአብሔር እጥፍ ድረብ አድርጎ እንዲሰጣች ሁ እንመኛለን። አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የተመሰገነ ይሁን።