የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ልዩ ማሳሰቢያ

የተወደዳችሁ የደ/ም/ቅ/ ሚካኤል ካቴድራል አባላት በያላችሁበት ሰላመ እግዚአብሄር ይድረሳችሁ!

የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ወረርሽኙ ትልቅ ስጋት በመሆኑ በዲሲ ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ግዛቶች የአደጋ ጊዜ አስቸኳይ አዋጅ ከመታወጁም በላይ ትላንት ማምሻውን አዋጁ በመላ ሀገሪቱ ሁሉ እንዲሆን ተወስኗል። በዚህ መሰረት የሃገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ በሰጡት መንፈሳዊ መመሪያና ቦርዱም ባለፈው እሁድ አሳሳቢነቱን እያየን ውሳኔዎች እናስተላልፋለን ባለው መሰረት ወረርሽኙን ለመከላከል እንዲቻል ውሳኔ ተላልፏል:: ይህም ምዕመናን ሁሉ ከዛሬ ቅዳሜ 03/14/2020 ጀምሮ ከነቤተሰቦቻችሁ ለሚቀጥሉት 3 እሁዶች በቤታችሁ ሆናችሁ በጾምና በጸሎት ይህንን ክፉ ጊዜ እንድታሳልፉ ተወስኗል:: ለዚሁ ተፈጻሚነት ሁላችንም በየቤታችን ሆነን የሱባኤውን ጊዜ በፆም በፀሎት ተጠምደን ከ3 እሁዶች በኋላ እንድንገናኝ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።  የሀገረ ስብከቱን መመሪያም ከዚህ በታች ማያያዛችንን እንገልጻለን።


የእግዚአብሔር ጥበቃውና ረድኤቱ
ከሁላችን ጋር ይሁን !

የደ/ም/ቅ/ ሚካኤል ካቴድራል አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ (ቦርድ)