እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን!!!!!

በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካቴድራል የጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን እንላለን!!!!

እንደሚታወቀው ሰንበት ትምህርት ቤታችን በዛሬው ዕለት በጌታ ትንሣኤ ከካህናት አባቶቻችንን ጋር የቆየ የምሳ መርሐ ግብር ልማድ ነበረን። ሆኖም ዓለምን ባስጨነቀው ወረርሺኝ ምክንያት እንደ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን መርሐ ግብሮች እንደተለመደው ማካሄድ አልተቻለም። በመሆኑም እግዚአብሔር በምሕረቱ ጎብኝቶን ወደ ቀደመ ወደምንናፍቀው አገልግሎታችን እንዲመልሰን እየተማጸንን ይህቺን አጭር መልክእት በአባላቱ ስም እናስተላልፋለን።

የ2020 የደብረ ዘይት በዓል

የ2012 ደብረ ዘይት በዓል በኮሮና ወረርሺን ምክንያት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል እንደ ሎሎቹ የዲሲና አካባቢው አብያተ ክርስቲያናት መንግሥት ባወጣው የብዙኀንን መሰባሰብ በሚያግደው መመሪያ መሠረት ለአገልግሎት በመዘጋቱ ቅዳሴው በካህናት ብቻ ተከናውኖ ለምዕመኑ በድረ ገጽ ቀጥታ ስርጭት ከኪዳን ጀምሮ እስከ ስብከተ ወንጌል የነበረው አገልግሎት ተላልፏል።ይህ በቤተ ክርስቲያኑ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ከአቅም በላይ በሆነ አየር ንብረት ማለትም ከከባድ በረዶ መውረድ ውጪ የቤተ ክርስቲያኑ(ካቴድራሉ)ለአገልግሎት ለምዕመናን ክፍት ያልሆነበት ጊዜ ይህ የመጀመርያው ነው። ይህ ክስተት ማለትም ወረርሺኙ እስከ አሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር ያልሆነ ስለሆነ ምዕመናን መች ተመልሰው በቤተ ክርስቲያን በአካል ተገኝተው አገልግሎት መካፈል እንደሚችሉ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው መንግሥታዊ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች ሁሉ ተዘግተዋል አሊያም አገልግሎት ቀንሰዋል። በመላው የተባበሩት አሜሪካ ግዛቶችም ያሉ ሕዝብ ሁሉ በዚህ ዓይነት ሁናቴ ላይ ይገኛሉ።
በመሆኑም ለሚቀጥሉትም ሳምንታት ይህ መሰሉ አገልግሎት እንደሚቀጥል ይታመናል። ልዑል አምላክ በይቅርታው ተመልክቶ መፍትሔ እንዲሰጠን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን!