የ2020 የደብረ ዘይት በዓል

የ2012 ደብረ ዘይት በዓል በኮሮና ወረርሺን ምክንያት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል እንደ ሎሎቹ የዲሲና አካባቢው አብያተ ክርስቲያናት መንግሥት ባወጣው የብዙኀንን መሰባሰብ በሚያግደው መመሪያ መሠረት ለአገልግሎት በመዘጋቱ ቅዳሴው በካህናት ብቻ ተከናውኖ ለምዕመኑ በድረ ገጽ ቀጥታ ስርጭት ከኪዳን ጀምሮ እስከ ስብከተ ወንጌል የነበረው አገልግሎት ተላልፏል።ይህ በቤተ ክርስቲያኑ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ከአቅም በላይ በሆነ አየር ንብረት ማለትም ከከባድ በረዶ መውረድ ውጪ የቤተ ክርስቲያኑ(ካቴድራሉ)ለአገልግሎት ለምዕመናን ክፍት ያልሆነበት ጊዜ ይህ የመጀመርያው ነው። ይህ ክስተት ማለትም ወረርሺኙ እስከ አሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር ያልሆነ ስለሆነ ምዕመናን መች ተመልሰው በቤተ ክርስቲያን በአካል ተገኝተው አገልግሎት መካፈል እንደሚችሉ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው መንግሥታዊ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች ሁሉ ተዘግተዋል አሊያም አገልግሎት ቀንሰዋል። በመላው የተባበሩት አሜሪካ ግዛቶችም ያሉ ሕዝብ ሁሉ በዚህ ዓይነት ሁናቴ ላይ ይገኛሉ።
በመሆኑም ለሚቀጥሉትም ሳምንታት ይህ መሰሉ አገልግሎት እንደሚቀጥል ይታመናል። ልዑል አምላክ በይቅርታው ተመልክቶ መፍትሔ እንዲሰጠን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን!